የኮቪድ-19 ምልክቶች

በአብዛኛው ጊዜ የሚታዩ የኮቪድ-19 ምልክቶች፡

🤒 ትኩሳት

😴 ድካም

🤧 ደረቅ ሳል

አንዳንድ በሽተኞች ህመም ሊሰማቸው ይችላል፤ የአፍንጫ መደፈን ወይም ፈሳሽ መብዛት የጉሮሮ ህመም እና ተቅማጥ ሊኖራቸው ይችላል

በአብዛኛው እነዚህ ምልክቶች መለስተኛ እና ቀስ በቀስ መታየት የሚጀምሩ ናቸው፤ አንዳንድ ሰዎች በበሽታው ቢያዙም እነዚህ ምልክቶችም ሆኑ የህመም ስሜት ላይሰማቸው ይችላል

ብዙ ሰዎች (80% ያህል) የተለየ ህክምና ሳያስፈልጋቸው ከበሽታው ሊያገግሙ ይችላሉ በኮቪድ-19 ከሚያዙ ሰዎች አንድ ስድስተኛ የሚሆኑት በጠና ታመው የመተንፈስ እክል ያጋጥማቸዋል

በእድሜ የገፉ ሰዎች እና እንደ ደም ግፊት፥ የልብ ወይም የስዃር በሽታ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች በጠና ሊታመሙ ይችላሉ

Source: Ministry of Health, Ethiopia

የኮሮና ቫይረስ እውነታዎች ኮሮና ቫይረስ በቤት ውስጥ ማከም